የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የይ​ሁዳ ንጉሥ አካዝ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፣ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዘጠኝ ዓመትም ገዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አካዝ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አካዝ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ንጉሥ ሆነ፤ ዘጠኝ ዓመትም ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 17:1
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዖ​ዝ​ያ​ንም ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም በሃ​ያ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮ​ሜ​ልዮ ልጅ በፋ​ቁሔ ላይ ዐመ​ፀ​በት፤ መት​ቶም ገደ​ለው፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።


በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ አካዝ ነገሠ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ እንደ ነበ​ሩት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አል​ሆ​ነም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካዝ ልጅ ሕዝ​ቅ​ያስ ነገሠ።