Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በዖ​ዝ​ያ​ንም ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም በሃ​ያ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮ​ሜ​ልዮ ልጅ በፋ​ቁሔ ላይ ዐመ​ፀ​በት፤ መት​ቶም ገደ​ለው፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዚያም የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ አሤረበት፤ አደጋ ጥሎም ገደለው፤ የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በነገሠ በሃያኛው ዓመትም ሆሴዕ በፋቁሔ እግር ተተክቶ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የዖዝያ ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የዖዝያ ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በዖዝያንም ልጅ በኢዮአታም በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ ተማማለ፤ መትቶም ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 15:30
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የይ​ሁዳ ንጉሥ አካዝ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ክፋት የተ​ነሣ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ጋም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይጥ​ሉ​ታል።


ሰማ​ርያ ንጉ​ሥ​ዋን እንደ ጥራጊ በውኃ ላይ ጣለ​ችው።


አሁ​ንም፥ “ንጉሥ የለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ራ​ን​ምና፤ ንጉ​ሥስ ምን ያደ​ር​ግ​ል​ናል?” ይላሉ።


“እኒህ ሕዝብ በቀ​ስታ በሚ​ሄ​ደው በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ቍርጥ ምክ​ርን መከሩ፤ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ያነ​ግ​ሡ​ላ​ቸው ዘንድ ይወ​ዳ​ሉና።


በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ አካዝ ርዳታ ፈልጎ ወደ አሦር ንጉሥ ላከ፤


በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ አካዝ ነገሠ።


የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰ​ማ​ር​ያም በን​ጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአ​ር​ጎ​ብና ከአ​ርያ ጋር መታው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።


የኢ​ያ​ቢ​ስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎ​ችም ከዱት፤ በይ​ብ​ል​ዓም መት​ተው ገደ​ሉት፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


የቀ​ረ​ውም የፋ​ቁሔ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች