የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
1 ሳሙኤል 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱም ሳኦል የሚባል የተመረጠ መልካም ልጅ ነበረው፤ በምድር ሁሉ ላይ ከእስራኤል ልጆች ከእርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰው አልነበረም፤ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻውና ከዚያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነት ተወዳዳሪ የማይገኝለት፥ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፥ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቂስም በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሳኦል ተብሎ የሚጠራ ልጅ ነበረው፤ ሳኦልም ከትከሻው ዘለል፥ በቁመት ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ መለል ያለ ነበር፤ በመልከቀናነቱም ከሁሉ ይበልጥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርሱም ሳኦል የሚባል የተመረጠ መልካም ልጅ ነበረው፥ ከእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰው አልነበረም፥ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻውና ከዚያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ። |
የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
በዚያም ግዙፋን የሆኑትን አየን፤ እኛም በእነርሱ ፊት እንደ አንበጣዎች ሆን፤ እንዲሁም በፊታቸው ነበርን፤” እያሉ የሰለሉአትን ምድር ለእስራኤል ልጆች አስፈሪ አደረጓት።
የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፤ ዕጣውም በማጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማጥርንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፤ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለገውም፤ አላገኘውምም።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።
የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሡና ሄዳችሁ አህዮችን ፈልጉ” አለው።