Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሳ​ኦ​ልም አባት የቂስ አህ​ዮች ጠፍ​ተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦ​ልን፥ “ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ወስ​ደህ ተነ​ሡና ሄዳ​ችሁ አህ​ዮ​ችን ፈልጉ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፣ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የሳኦል አባት ቂስ፥ አህዮቹ ጠፍተውበት ነበር፤ ስለዚህም ልጁን ሳኦልን “ከአገልጋዮች አንዱን ይዘህ ሂድና የጠፉትን አህዮች ፈልግ” ብሎ አዘዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፥ ቂስም ልጁን ሳኦልን፦ ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሣ፥ አህዮችንም ለመሻት ሂድ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 9:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሠ​ላሳ ሁለት የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ይቀ​መጡ የነ​በሩ ሠላሳ ሁለት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች የተ​ባሉ በገ​ለ​ዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተ​ሞች ነበ​ሩ​አ​ቸው።


በነ​ጫጭ አህ​ዮች ላይ የም​ት​ጫኑ፥ በፍ​ርድ ወን​በር ላይ​የ​ም​ት​ቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም የም​ት​ሄዱ በቃ​ላ​ችሁ ተና​ገሩ።


ከቤተ ሰቡም አንዱ እር​ሱ​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን፥ “ወዴት ሄዳ​ችሁ ኖሮ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አህ​ዮ​ችን ልን​ፈ​ልግ ሄደን ነበር፤ ባጣ​ና​ቸ​ውም ጊዜ ወደ ሳሙ​ኤል መጣን” አሉት።


ዛሬ ከእኔ በተ​ለ​የህ ጊዜ በብ​ን​ያም ግዛት በቤ​ቴል አው​ራጃ በራ​ሔል መቃ​ብር አጠ​ገብ ሁለት ሰዎች እየ​ቸ​ኰሉ ሲሄዱ ታገ​ኛ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፦ ልት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ሂዳ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​ላ​ቸው አህ​ዮች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ አባ​ትህ ስለ አህ​ዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የል​ጄን ነገር እን​ዴት አደ​ር​ጋ​ለሁ? እያለ ስለ እና​ንተ ይጨ​ነ​ቃል ይሉ​ሃል።


ለእ​ር​ሱም ሳኦል የሚ​ባል የተ​መ​ረጠ መል​ካም ልጅ ነበ​ረው፤ በም​ድር ሁሉ ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ርሱ ይልቅ መል​ካም የሆነ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ከት​ከ​ሻ​ውና ከዚ​ያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።


ከሦ​ስት ቀንም በፊት የጠፉ አህ​ዮ​ችህ ተገ​ኝ​ተ​ዋ​ልና ልብ​ህን አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው። የእ​ስ​ራ​ኤል መል​ካም ምኞት ለማን ነው? ለአ​ን​ተና ለአ​ባ​ትህ ቤት አይ​ደ​ለ​ምን?” አለው።


ወደ ተራ​ራ​ማ​ውም ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲ​ልካ ምድ​ርም አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም፤ በፋ​ስ​ቂም ምድር አለፉ፤ በዚ​ያም አል​ነ​በ​ሩም፤ በኢ​ያ​ሚ​ንም ምድር አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች