Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የብ​ን​ያ​ም​ንም ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በማ​ጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማ​ጥ​ር​ንም ወገን በየ​ሰዉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በቂስ ልጅ በሳ​ኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለ​ገ​ውም፤ አላ​ገ​ኘ​ው​ምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጐሣው ወደ ፊት አቀረበ፤ የማጥሪ ጐሣም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ። እርሱ ግን ተፈልጎ አልተገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየወገኑ ወደ ፊት አቀረበ፤ የማጥሪ ቤተሰብም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ። እርሱ ግን ተፈልጎ አልተገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እንደገናም ሳሙኤል፥ የብንያም ነገድ ቤተሰቦች ሁሉ ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከነዚያም የማጥሪ ቤተሰብ በዕጣ ተመረጠ፤ በመጨረሻም የማጥሪ ቤተሰብ ወንዶች ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከእነርሱም መካከል ለቂስ ልጅ ለሳኦል ዕጣ ወጣ፤ እነርሱም በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፥ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 10:21
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አበ​ኔ​ርም ደግሞ በብ​ን​ያም ልጆች ጆሮ ተና​ገረ፤ አበ​ኔ​ርም ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በብ​ን​ያም ቤት ሁሉ መል​ካም የነ​በ​ረ​ውን ለዳ​ዊት ሊነ​ግ​ረው ወደ ኬብ​ሮን ሄደ።


ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ።


ከዚ​ያም ወዲያ ንጉሥ ያነ​ግ​ሥ​ላ​ቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው የቂ​ስን ልጅ ሳኦ​ልን አርባ ዓመት አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው።


ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች ሁሉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በብ​ን​ያም ወገን ላይ ወደቀ።


ሳሙ​ኤ​ልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካ​ከል ተሸ​ሽ​ጎ​አል” ብሎ መለሰ።


ለእ​ር​ሱም ሳኦል የሚ​ባል የተ​መ​ረጠ መል​ካም ልጅ ነበ​ረው፤ በም​ድር ሁሉ ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ርሱ ይልቅ መል​ካም የሆነ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ከት​ከ​ሻ​ውና ከዚ​ያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች