የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደ ግብጻውያንና እንደ ፈርዖን ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱም እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የግብጽ ንጉሥና ግብጻውያን እንዳደረጉት ስለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እስራኤላውያን የግብጽን ምድር ለቀው የወጡት፥ እግዚአብሔር ግብጻውያንን በብርቱ ከቀጣቸው በኋላ አልነበረምን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ግብጻውያንና ፈርዖንም ልባቸውን እንዳጸኑ ልባችሁን ለምን ታጸናላችሁ? እግዚአብሔር ኃይሉን ካደረገባቸው በኋላ ያወጡአቸው አይደሉምን? እነርሱም አልሄዱምን?

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 6:6
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስሙ ክብ​ርን አምጡ፤ መሥ​ዋ​ዕት ያዙ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ግቡ።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እነ​ሆም፥ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ይገ​ባሉ፤ በፈ​ር​ዖ​ንና በሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቹም ላይ እከ​ብ​ራ​ለሁ።


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም ሁሉ እያ​ሳ​ደዱ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር መካ​ከል ገቡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ መስ​ማ​ት​ንም እንቢ አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ይ​ለ​ቅቅ የፈ​ር​ዖን ልብ ደነ​ደነ።


ፈር​ዖ​ንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ፈር​ዖ​ንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደ​ነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


ፈር​ዖ​ንም ዝናቡ፥ በረ​ዶ​ውም፥ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደ​ልን ጨመረ፤ እር​ሱና ሹሞ​ቹም ልባ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


ዛሬ የሚ​ባ​ለው ቀን ሳለ ከእ​ና​ንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢ​አት በሚ​ያ​ደ​ርስ ስሕ​ተት እን​ዳ​ይ​ጸና ሁል​ጊዜ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን መር​ምሩ።