የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለጦ​ር​ነት ሰበ​ሰቡ፤ ራሳ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ በሰ​ኮት ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሰ​ኮ​ትና በዓ​ዜቃ መካ​ከል በኤ​ፌ​ር​ሜም ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍልስጥኤማውያን ሰራዊታቸውን ለጦርነት አሰባስበው፣ በይሁዳ ምድር በሦኮን ላይ አከማቹ፤ እነርሱም በሰኰትና በዓዜቃ መካከል ባለው በኤፌሰደሚም ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለጦርነት አሰባስበው፥ በይሁዳ ምድር በሰኮ ላይ አከማቹ፤ በሰኮና በዓዜቃ መካከል ባለው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍልስጥኤማውያን ሶኮ ተብላ በምትጠራው በይሁዳ ለጦርነት ተሰለፉ፤ እነርሱም በሶኮና በዐዜቃ መካከል ኤፌስዳሚም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፍረው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን በይሁዳ ባለው በሰኮት አከማቹ፥ በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በአርፌስደሚም ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 17:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ከዳ​ዊት ጋር በፋ​ሶ​ደ​ሚን ነበረ፥ በዚ​ያም ገብስ በሞ​ላ​በት እርሻ ውስጥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለሰ​ልፍ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ።


ቤተ​ሱ​ራን፥ ሱላ​ኮን፥ ዓዶ​ላ​ምን፥


ደግ​ሞም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቆ​ላ​ውና በደ​ቡብ በኩል ባሉት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና ኤሎ​ንን፥ ጋቤ​ሮ​ት​ንም፥ ሠካ​ዕ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ቴም​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም፥ ጋማ​ዚ​እ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወስ​ደው በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የቀ​ሩ​ትን የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ፥ ለኪ​ሶ​ንና አዚ​ቃ​ንም ይወጋ ነበር። እነ​ዚህ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች በይ​ሁዳ ከተ​ሞች መካ​ከል ቀር​ተው ነበ​ርና።


ኤር​ሙት፥ ኤዶ​ላም፥ ሜም​ብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤


እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።


ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከመ​ከ​ተል ተመ​ለሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ስፍ​ራ​ቸው ሄዱ።


በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዘመቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሰም​ተው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ፈሩ።