“በሩቅ አገር የሚኖር የውጪ አገር ሰው የስምህን ገናናነትና ለሕዝብህ ያደረግኸውን ድንቅ ነገር ሁሉ ሰምቶ፥ በዚህ ቤተ መቅደስ ሊያመልክህና ሊጸልይ ቢመጣ፥
ኢያሱ 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ይህን ታሪክ ነገሩት፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በግብጽ ያደረገውን ሁሉ ስለ ሰማን እኛ የመጣነው በጣም ሩቅ ከሆነ አገር ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “እኛ ባሪያዎችህ የአምላካህን የእግዚአብሔርን ዝና ሰምተን፣ እጅግ ሩቅ ከሆነ አገር መጥተናል፤ ዝናውንና በግብጽ ያደረገውንም ሁሉ ሰምተናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “ከአምላክህ ከጌታ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር ባርያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብጽም ያደረገውን ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉት፥ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብፃውያንም ያደረገውን ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉት፦ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር ባሪያዎችህ መጥተናል፥ ዝናውንም፥ በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥ |
“በሩቅ አገር የሚኖር የውጪ አገር ሰው የስምህን ገናናነትና ለሕዝብህ ያደረግኸውን ድንቅ ነገር ሁሉ ሰምቶ፥ በዚህ ቤተ መቅደስ ሊያመልክህና ሊጸልይ ቢመጣ፥
ኢያሱ፥ ቃድሚኤል፥ ባኒ፥ ሐሸባንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሸባንያና ፐታሕያ ተብለው የሚጠሩት ሌዋውያን፦ “ተነሥታችሁ በመቆም ዘለዓለማዊውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ከምስጋናና ከበረከት ሁሉ በላይ፥ ከፍ ከፍ ይበል! በሉ” አሉአቸው።
እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።
ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤
እንግዲህ ከምትኖርበት ምድር ርቀው የሚገኙትንና በቅርብ ለሚገኙ ሕዝቦች ንብረት ያልሆኑ ከተሞችን በኀይል በምትይዝበት ጊዜ የምትወስደው እርምጃ ይኸው ነው።
እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በነበሩት በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል፤ እነዚህም ሁለቱ ነገሥታት በዐስታሮት ይኖሩ የነበሩት የሐሴቦን ንጉሥ ሲሖንና የባሳን ንጉሥ ዖግ ናቸው።
ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ጌታችን ሆይ! እኛ አገልጋዮችህ በእርግጥ ይህን አድርገናል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተ በውስጧ የሚኖሩትን ሕዝብ በመግደል ምድሪቱን ያወርሳችሁ ዘንድ አገልጋዩን ሙሴን ያዘዘው መሆኑን ዐውቀናል፤ ይህንንም ያደረግነው እናንተን ከመፍራታችን የተነሣ ሕይወታችንን ለማትረፍ ፈልገን ነው።