ሙሴም ኢያሱን “ጥቂት ሰዎች ምረጥና በነገው ዕለት ዐማሌቃውያንን ውጋ፤ እኔም ተአምራት እንድፈጽምባት እግዚአብሔር የሰጠኝን በትር ይዤ በኮረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ” አለው።
ኢያሱ 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም፥ ኢያሱ ከወታደሮቹ ጋር በዐይ ላይ ዘመተ፤ ከሠራዊቱም የተሻለ ችሎታ ያላቸውን ሠላሳ ሺህ ወታደሮች መርጦ በሌሊት ሲልካቸው አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱና ሰራዊቱ በሙሉ ጋይን ለመውጋት ወጡ፤ ኢያሱም ምርጥ ከሆኑት ተዋጊዎቹ ሠላሳ ሺሕ ጦር አዘጋጅቶ በሌሊት ላካቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ተዋጊዎቹም ሁሉ ወደ ጋይ ሊወጡ ተነሡ፤ ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ በሌሊትም ሰደዳቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ ተዋጊዎቹም ሕዝብ ሁሉ ተነሥተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያሱም ጽኑዓን፥ ተዋጊዎችና ኀያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌሊትም ላካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ሰልፈኞቹም ሁሉ ወደ ጋይ ሊወጡ ተነሡ፥ ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ በሌሊትም ሰደዳቸው፥ |
ሙሴም ኢያሱን “ጥቂት ሰዎች ምረጥና በነገው ዕለት ዐማሌቃውያንን ውጋ፤ እኔም ተአምራት እንድፈጽምባት እግዚአብሔር የሰጠኝን በትር ይዤ በኮረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ” አለው።
ከዚህ በፊት በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ የደረሰውን ጥፋት በዐይና በንጉሥዋም ላይ ደግሞ ትፈጽምባቸዋለህ፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከእርስዋ የሚገኘውን የንብረትና የከብት ምርኮ ለራሳችሁ ታደርጋላችሁ፤ ከኋላ በኩል በከተማይቱ ላይ በድንገት አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።”
እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፦ “ከከተማይቱ በስተኋላ አድፍጣችሁ ቈዩ፤ ይሁን እንጂ ከከተማይቱ ብዙ ሳትርቁ አደጋ ለመጣል በሚያስችላችሁ ሁኔታ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ፤
የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያን ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ፍጥረት ሁሉ በእሳት ተቃጥሎ ይጠፋል። ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል፤