ኢያሱ 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታፑሐ ዙሪያ የሚገኘውም ምድር ለምናሴ ተሰጠ፤ በድንበር ላይ የምትገኘው ትንሽዋ የታፑሐ ከተማ ግን የኤፍሬም ዘሮች ይዞታ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታጱዋ ምድር የምናሴ ይዞታ ነበር፤ ይሁን እንጂ በድንበሩ ላይ የምትገኘው የታጱዋ ከተማ የኤፍሬም ዘሮች ይዞታ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ግን ለኤፍሬም ልጆች ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጣፌት ምድር ለምናሴ ነበረ፤ ጣፌት ግን በኤፍሬም ልጆችና በምናሴ ልጆች አውራጃ ያለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፥ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ግን ለኤፍሬም ልጆች ሆነ። |
ይኸው ድንበር በምዕራብ በኩል ከታፑሐ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርስና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ ለኤፍሬም ነገድ በየወገኑ ርስት ሆኖ የተሰጠው ምድር ይህ ነበር።
የምናሴ የርስት ይዞታ ከአሴር ተነሥቶ በሴኬም በስተ ምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ሚክመታት ይደርስ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በማለፍ የዔንታፑዓሕን ሕዝብ ይጨምራል፤