የምታፈቅረው ጽድቅን ከሆነ መልካም ምግባር የሥራዋ ፍሬ ነው፤ ቁጥብነትንና ጥንቁቅነትን፥ ፍትሕንና ጽናትንም የምታስተምር እርሷ ነችና።
እውነትን የወደደ ሰውም ቢኖር በእርሷ ነው፤ ድካሟ ያማረ ነውና፥ ንጽሕናንና ጥበብን፥ እውነትንና ብርታትን፥ ትሩፋትንና ደግነትንም ታስተምራለች። በዓለሙ ውስጥም በሰው ሕይወት ከእርሷ የሚሻልና የሚጠቅም ምንም የለም።