ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ሰፊ ተሞክሮ ለማግኘት የጓጓም ካለ፥ ያለፈውን ታውቃለች፥ መጪውንም ትተነቢያለች፤ ምሳሌዎችን የምትተረጉም፥ እንቆቅልሾችን የምትፈታ ነች፤ ምልክቱንና ድንቅ ነገሮችን፥ የዓመታትና የዘመናትንም አመጣጥ ታውቃለች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ብዙ ዕውቀትንና ደግነትን ያወቀ ሰው ቢኖር በእርሷ ነው፤ የቀደመውንና የሚመጣውንም ሥራ ያወቀ ሰው ቢኖር በእርሷ ነው፤ የነገር መልስንና ፈጥኖ መተርጐምን ቢያውቅም በእርሷ ነው፤ ተአምራትንና ድንቆችን፥ የጊዜያትንና የዓመታትንም መለዋወጥ አስቀድሞ ቢያውቅ በእርስዋ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |