ጥበብ አዋቂ፥ ቅዱስ፥ የተለየ ባለ ብዙ ባሕርይ ረቂቅ፥ ተንቀሳቃሽ፥ አስተዋይ፥ እንከን የለሽ፥ ግልጽ፥ የማትደፈር፥ ቅን፥ ብልኀ፥
በእርስዋ የማስተዋል መንፈስ አለና፤ እርሱም ቅዱስ፥ በልደት ብቸኛ የሆነ፥ አንድ ሲሆን ሀብቱ ብዙ የሆነ፥ ረቂቅ፥ እንቅስቃሴውም የፈጠነ፥ ቃሉ የሚያምር፥ ጠቢብ፥ ዕድፈትም የሌለበት፥ የማይደክም፥ ጥንት የሌለው፥ ነዋሪ፥ ቸርነትን የሚወድ፥ ፈጣን፥ በጎ ነገርን ለማድረግ የሚከለክለው የሌለ፥