ንጽሕት የሆነች፥ የኀጢአትንም አልጋ የማታውቅ መኻን ሴት፥ የተባረከች ነች፤ ነፍሶች በሚጐበኙበት ጊዜ ፍሬን ታገኛለች።
ነውር የሌለባት፥ የኀጢአት ምንጣፍ የማታውቅ መካን ሴት ብፅዕት ናት፥ ከኀጢአትም የነጻች ናት፥ ይህች እንዲህ ያለችው ሴት ነፍሳት በሚጐበኙበት ጊዜ ፍሬ ታገኛለች።