እርሱ ከማንም የበለጠ መበደሉን ራሱ ያውቀዋል፥ ከአንድ ዓይነት አፈር ተሰባሪ ሸክላና ጣኦቶችን የሚሠራ ነውና።
ይህም ከሁሉ ፈጽሞ እንደሚበድል ታወቀ፥ በምድር ከሚታየውና ፈጥኖ ከሚጠፋው ከእንጨት የተቀረፀ ጣዖትን ሠርትዋልና።