የክፉ ሰዎችን በደል የሚከታተሉት፥ የሚምሉባቸው ጣኦቶች ሳይሆኑ፥ ለኃጡአተኞች የተወሰነው ቅጣት ነው።
በኀጢአታቸው የተፈረደባቸውን ፍርድ ለማስተላለፍ ነው እንጂ ኀይሉን ይገልጥብናል ሲሉ የማሉ አይደለምና፤ እንግዲህ ሁልጊዜ ሰውን በሚበድሉ ሰዎች ወንጀል ላይ ፍርድ ትምጣባቸው።