ልጁ ዓሣውን ቀዶ ከፈተውና ሐሞቱን፥ ልቡንና ጉበቱን ወሰደ፥ ከዚህ በኋላ ዓሣውን ጠበሰና በሉት፤ የቀረውን ለጉዞ በጨው ቀመመው፤ መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ወደ ሜዶንም ተቃረቡ።
ያም ልጅ መልአኩን አለው፥ “አንተ ወንድሜ አዛርያ! የዚህ ዓሣ ልቡ፥ ጉበቱና ሐሞቱ ለምንድን ነው?”