መጽሐፈ ጦቢት 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምግቡ ቀረበልኝ፥ የተትረፈረፈ ምግብ እንደቀረበልኝ ባየሁ ጊዜ ልጄን ጦብያን እንዲህ አልሁት፦ “ልጄ ሆይ ሂድና ወደ ነነዌ ተማርከው ከመጡት ወንደሞቻችን መካከል የሆኑትንና ታማኝ ልቦና ያላቸውን ድኻ የሆኑትን ሰዎች ፈልግና ከማዕዴ እንዲካፈሉ አምጣቸው፤ ልጄ ሆይ እስክትመለስ እጠብቅሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምግቡም እጅግ ብዙ እንደ ሆነ ባየሁ ጊዜ ልጄን እንዲህ አልሁት፥ “ሄደህ ከወንድሞቻችን ያገኘሃቸውን ድኆች ባልንጀሮችን አምጣ። እግዚአብሔርን አስቤዋለሁና። እነሆ እኔም እጠብቅሃለሁ።” |