ጠባቂዬ፥ ደጋፊዬም ነበርክና ሥጋዬንም ከጥፋት፥ ከዋሾ ምላስ ወጥመድ፥ ሐሰትን ከሚፈጥሩ ከንፈሮች አድነሃልና፥ በጠላቶቼ ፊት ከጐኔ ቆምህ፤ ደግፈኸኝ አዳንከኝም።
ረድተኸኛልና፥ ሰውረኸኝማልና፥ ሰውነቴንም ከሞት አድነኸዋልና፥ ከአንደበት የነገር ሥራ ወጥመድም አድነኸኛልና፥ ሐሰትንም ከሚሠሩአት ከብዙ ሰዎች ምላስ አድነኸኛልና፥ በጠላትነትም ከተነሡብኝ ሰዎች ፊት የምትረዳኝና የምትሰውረኝ ሆነሃልና።