ጌታዬ፥ የጌታዬንም አባት ተጣራሁ፤ በመከራ ጊዜ፥ ረዳት በማይገኝበት በትዕቢተኛውም ዘመን አትተወኝ፤ ስምህን ያለማቋረጥ አመሰግናለሁ፤ የምስጋና መዝሙርም እዘምርለታለሁ ብዬ ለመንሁህ።
አባቴና ጌታዬ እግዚአብሔርንም፥ ረዳት በሌለበት፥ ትዕቢተኞች በተነሡበት ወራት በመከራዬ ጊዜ አትለየኝ አልሁት።