ሩት 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፥ ቦዔዝም፦ “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ሩት እስኪነጋ ድረስ እግርጌው ተኛች፤ ዳሩ ግን ማንም ሰው ተለይቶ ሊታወቅ በማይችልበት ሰዓት ቀደም ብላ ተነሣች፤ እርሱም፣ “ሴት ወደዚህ ዐውድማ መምጣቷ እንዳይታወቅ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሩት በቦዔዝ እግር አጠገብ ተኛች፤ ነገር ግን ቦዔዝ ወደ ዐውድማው እንደ መጣች ማንም እንዲያውቅ ስላልፈለገ ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፣ ቦዔዝም፦ ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ ብሎ ነበርና ገና ሰውና ሰው ሳይተያይ ተነሣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፤ ቦዔዝም “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ፤” ብሎ ነበርና ገና ሰውና ሰው ሳይተያይ ተነሣች። |
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
እርሱም፦ “የለበስሽውን ልብስ አምጥተሽ ያዥው” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፍሮላት አሸከማት። እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ።