ሩት 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፣ ቦዔዝም፦ ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ ብሎ ነበርና ገና ሰውና ሰው ሳይተያይ ተነሣች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ስለዚህም ሩት እስኪነጋ ድረስ እግርጌው ተኛች፤ ዳሩ ግን ማንም ሰው ተለይቶ ሊታወቅ በማይችልበት ሰዓት ቀደም ብላ ተነሣች፤ እርሱም፣ “ሴት ወደዚህ ዐውድማ መምጣቷ እንዳይታወቅ” አላት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፥ ቦዔዝም፦ “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ስለዚህ ሩት በቦዔዝ እግር አጠገብ ተኛች፤ ነገር ግን ቦዔዝ ወደ ዐውድማው እንደ መጣች ማንም እንዲያውቅ ስላልፈለገ ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፤ ቦዔዝም “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ፤” ብሎ ነበርና ገና ሰውና ሰው ሳይተያይ ተነሣች። ምዕራፉን ተመልከት |