ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
መዝሙር 94:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ተነሥ፥ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ የምድር ዳኛ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የዓለም ፈራጅ ነህ፤ ስለዚህ ተነሥ፤ ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ቅጣት ስጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእምነት ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤ |
ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።