መዝሙር 77:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ ሥራህንም አሰላስላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ፥ አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፤ ውኆችን እንደ ረዋት ውኃ አቆመ። |
ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?