እኔን ለመጠየቅ የሚገባ ከንቱን ይናገራል፥ ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት፥ ወደ ውጭ ይወጣል ይናገራልም።
ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤ እንዲህ እያሉም፣ የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤
የሚጠሉኝ ሁሉ በእኔ ላይ በሹክሹክታ ይናገራሉ፤ ክፉ ነገር እንዲደርስብኝም ያቅዳሉ።
በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራዋለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
እንደ ሞተ ሰው ከልብ ተረሳሁ፥ እንደ ተበላሸ ዕቃም ሆንሁ።
ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፥ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።
እንጨት ባለቀ ጊዜ እሳት ይጠፋል፥ ጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላል።
ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በንግግሩ እንደሚያጠምዱት ተማከሩ።
በዐመፃ፥ በግፍ፥ በስስት፥ በክፋት፥ በቅናት፥ ነፍስ በመግደል፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በተንኮል የተሞሉ፥ የሚያሾከሹኩ፥
ወደ እናንት ስመጣ፥ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባት ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ ሐሜት፥ ማሾክሾክ፥ ኩራት፥ ሁከትም ይኖር ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።