Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 1:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በዐመፃ፥ በግፍ፥ በስስት፥ በክፋት፥ በቅናት፥ ነፍስ በመግደል፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በተንኮል የተሞሉ፥ የሚያሾከሹኩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ር​ሱም ዐመ​ፅን ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም፥ ምኞ​ት​ንም፥ ቅሚ​ያ​ንም፥ ቅና​ት​ንም የተ​መሉ ናቸው፤ ምቀ​ኞች፥ ነፍሰ ገዳ​ዮች፥ ከዳ​ተ​ኞች፥ ተን​ኰ​ለ​ኞች፥ ኩሩ​ዎች፥ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ግብ​ራ​ቸ​ው​ንም ያከፉ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 1:29
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔን ለመጠየቅ የሚገባ ከንቱን ይናገራል፥ ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት፥ ወደ ውጭ ይወጣል ይናገራልም።


ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፥ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።


እንጨት ባለቀ ጊዜ እሳት ይጠፋል፥ ጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።


እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “ጻድቅ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም፤


ወደ እናንት ስመጣ፥ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባት ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ ሐሜት፥ ማሾክሾክ፥ ኩራት፥ ሁከትም ይኖር ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።


እንዲሁም ሴቶች መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ሐሜተኞች ያልሆኑ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች