በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም፥ በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በመከራ ውስጥ ነኝና ማረኝ፤ ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል።
እግዚአብሔር ሆይ! በችግር ላይ ስለ ሆንኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ዐይኖቼ፥ ነፍሴና ሥጋዬ በሐዘን ደክመዋል።
ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤ ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።
ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።
በጨለማ በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥ በችግር በብረትም የታሰሩ፥
ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፥ ወድዶኛልና አዳነኝ።
አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
ለምንስ ፊትህን ትሰውራለህ? መከራችንንና ጭንቃችንን ለምን ትረሳለህ?
በመቃተቴ ደክሜአለሁ፥ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን በእንባ አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።
ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥ እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።
የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥ በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥ ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም።
ፌ። ዓይናችን ወደ ከንቱ ረዳታችን ገና ሲመለከት ጠፍቶአል፥ በመቆየታችን ማዳን የማይቻለውን ሕዝብ ጠብቀናል።
ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፥ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፥