37 አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
37 ጠላቶቼን አሳድጄ ያዝኋቸው፤ እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።
37 ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም።
አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፥ ለያዕቆብ መድኃኒትን እዘዝ።
አየሁም፤ እነሆም ነጭ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድል እየነሣ፥ ድልም ለመንሣት ወጣ።
ክፉዎቸ ግን ይጠፋሉ፥ የጌታ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት፥ እንደ ጢስም ተንነው ይጠፋሉ።
በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የጌታም መልአክ ያስጨንቃቸው።
ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
እደሰታለሁ፥ በአንተም ሐሤትን አደርጋለሁ፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም፥ በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ።