እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥ ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ።
በየአቅጣጫው የከበበኝን፣ አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
በዙሪያዬ የከበቡኝን በብዙ ሺህ የሚቈጠሩትን ጠላቶቼን አልፈራቸውም።
ከሚከብቡኝና በእኔ ላይ ከሚነሡ ከአእላፍ አሕዛብ አልፈራም።
እዚያም የእስራኤል ሠራዊት በዳዊት አገልጋዮች ተመታ፤ በዚያም ቀን ታላቅ እልቂት ሆነ፤ ሃያ ሺህም ሰዎችም ሞቱ።
የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በጌታና በመሢሑ ላይ ተማከሩ፦
በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።
በተኛህ ጊዜ አትፈራም፥ ስትተኛም፥ እንቅልፍህ የጣፈጠ ይሆንልሃል።
ስትሄድም ይመሩሃል፥ ስትተኛ ይጠብቁሃል፥ ስትነሣ ያነጋግሩሃል።
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?