መዝሙር 26:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋራ፣ ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋራ አታስወግዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤ ሕይወቴንም አታጥፋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ። |
በዳዊት ዘመነ መንግሥት፥ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፥ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።
እነርሱም እንዲህ ሲሉ ይመልሱለታል ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይም ተጠምተህ ወይም እንግዳ ሆነህ ወይም ታርዘህ ወይም ታመህ ወይም ታስረህ መቼ አየንህና አላገለገልንህም?’
ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፥ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በጌታ ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፥ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።