መዝሙር 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያም ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋል፥ አግዚአብሔር በጻድቃን ዘንድ ነውና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሉበት ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሚገኘው ከጻድቃን ጋር ስለ ሆነ እነርሱ በፍርሃት ይሸበራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም። |
ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ ጌታ ሆይ የገዛኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ በኃይልህ ታላቅነት፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፥ እንደ ድንጋይ ቀጥ አሉ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
በሰፈር በእርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።