የአሕዛብ ጣዖታት የብርና የወርቅ፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
የአሕዛብ ጣዖታት ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣ የሰው እጅ ያበጃቸው ናቸው።
የአሕዛብ አማልክት ከብርና ከወርቅ በሰው እጅ የተሠሩ ጣዖቶች ናቸው።
ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ፥ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
በዚያም ማየትም ሆነ መስማት፥ መብላት ሆነ ማሽተት የማይችሉትን፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ።