መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።
መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል። ሃሌ ሉያ።
መኻኒቱንም በቤቷ በክብር ያኖራታል፤ ልጆችንም በመስጠት ደስ ያሰኛታል። እግዚአብሔር ይመስገን!
ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ፥ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ምስጋናን እንስጥ
ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርሷ ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤
ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች።
እግዚአብሔር በቅዱስ መኖሪያው ወላጅ ለሞቱባቸው አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል ጌታ።
ይልቁንም ሴቲቱ ሳትረክስ ንጹሕ ብትሆን ከእርግማን የተጠበቀች ትሆናለች፥ ልጅንም መፀነስ ትችላች።
“አንቺ የማትወልጅ መካን! ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ! እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና” ተብሎ ተጽፎአልና።
ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል። መካኒቱ ሰባት ወለደች፥ ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች።