መዝሙር 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? “ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤ የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኞች በጨለማ አድብተው ልበቅኖችን ለመግደል ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ። |
ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።
ሳኦልም በልቡ፥ “ወጥመድ እንድትሆነው፥ በፍልስጥኤማውያንም እጅ እንዲጠፋ እርሷን እድርለታለሁ” ሲል አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን፥ “እነሆ፤ ዛሬ ዐማቼ ትሆናለህ” አለው።