Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 7:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የክፉዎች በደል ይጥፋ፥ ጻድቁን ግን አቅና፥ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጋሻዬ ልዑል አምላክ ነው፤ እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ልባቸው ቅን የሆኑትን የሚያድን፥ ልዑል እግዚአብሔር፥ እርሱ ጋሻዬ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት ይረ​ዳ​ኛል ልበ ቅኖ​ችን የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 7:10
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።


በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለው።


ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል።


ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፥ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።


አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።


ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።


ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።


የኃይላቸው ክብር አንተ ነህና፥ በሞገስህም ቀንዳችን ከፍ ከፍ ይላልና።


ልበ ጠማሞች በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፥ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው።


ቅኖች በምድር ላይ ይቀመጣሉና፥ ፍጹማንም በእርሷ ይኖራሉና፥


በቅንነት የሚሄድ ይድናል፥ በጠማምነት የሚሄድ ግን ወዲያው ይወድቃል።


ነገር ግን ኩላሊትንና ልብን የምትመረምር በቅንም የምትፈርድ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በእነርሱ ላይ የሚሆነውን በቀልህን ልይ።


“እኔ ጌታ ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ልብን እመረምራለሁ ኩላሊትንም እፈትናለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች