በዓይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥ በጣቱ ያስተምራል፥
በዐይኑ የሚጠቅስ፣ በእግሩ ምልክት የሚሰጥ፣ በጣቶቹ የሚጠቍም፣
እርሱም፥ ለማታለል በዐይኑ ይጠቅሳል፤ በእግሩ ያመለክታል፤ በእጁ ይጠቊማል።
በዐይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥ በጣቱ ጥቅሻ ያመለክታል፤
ልብህስ ለምን ወደ ሌላ ይወስድሃል? ዐይኖችህስ ለምን ይገላምጣሉ?
በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፥ ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ።
ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።
በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፥ ደፍሮ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል።
የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፥ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥