ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።
ይህም ልባምነትን ገንዘብ እንድታደርግ፣ ከንፈሮችህም ዕውቀትን እንዲጠብቁ ነው።
ይህን ብታደርግ አስተዋይነት ይኖርሃል፤ ንግግርህም ዕውቀት እንዳለህ ይገልጣል፤
መልካም ዐሳብን ትጠብቅ ዘንድ በከንፈሮቼ የማዝዝህን ዕወቅ።
ከአፍህ የሚወጡትን ፍርዶች ሁሉ በከንፈሮቼ ደገምኳቸው።
ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፥ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
መዘርዘር ከምችለው በላይ ቢሆንም፥ አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል።
የጻድቅ ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ይመግባሉ፥ አላዋቂዎች ግን ከማስተዋል ጉድለት የተነሣ ይሞታሉ።
የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል፥ የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል።
የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፥ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።
የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል።
ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቁ ይገኛል፥ የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።
ልጄ ሆይ፥ እነዚህ ከዐይኖችህ አይራቁ፥ መልካም ጥበብንና ጥንቃቄን ጠብቅ።
ሙሽራዬ ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ ማር ይንጠበጠባል፥ ከምላስሽ በታች ማርና ወተት አለ፥ የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው።