አትተዋት፥ ትጠብቅሃለች፥ ውደዳት፥ ትንከባከብህማለች።
ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤ አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች።
ጥበብን አትተዋት፤ እርስዋም ትጠብቅሃለች፤ ውደዳት፤ እርስዋም ከአደጋ ሁሉ ትከላከልልሃለች።
አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች።
ልጄ ሆይ፥ እነዚህ ከዐይኖችህ አይራቁ፥ መልካም ጥበብንና ጥንቃቄን ጠብቅ።
እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።
ሥር ሰዳችሁ፥ በፍቅርም ታንጻችሁ ክርስቶስ በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፥
እንዲሁም ለመዳን እውነቱን ወድደው ባለ መቀበላቸው ለሚጠፉት በማታለል ክፋት ሁሉ ይመጣባቸዋል።