ዳዊትም እንዲህ ብሏልና፦ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለጌታም የሚሠራው ቤት በአገሩ ሁሉ በስሙና በክብሩ እጅግ ታላቅና ዝነኛ ሊሆን ይገባል፤ እኔም ስለዚህ ዝግጅትን አደርጋለሁ።” ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ የግንባታ ቁሳቁስ አዘጋጀ።
ምሳሌ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም አንድ ጊዜ ከአባቴ ጋር የምኖር ትንሽ ልጅ ነበርኩ፤ ለእናቴም አንድ ነበርኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ፊት እወደድ ነበር። |
ዳዊትም እንዲህ ብሏልና፦ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለጌታም የሚሠራው ቤት በአገሩ ሁሉ በስሙና በክብሩ እጅግ ታላቅና ዝነኛ ሊሆን ይገባል፤ እኔም ስለዚህ ዝግጅትን አደርጋለሁ።” ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ የግንባታ ቁሳቁስ አዘጋጀ።
ንጉሡም ዳዊት ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በብቸኛነት እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ብላቴና ለጋ ነው፤ ሕንጻው ግን ለጌታ ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።