ምሳሌ 27:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፥ ነፍስም በወዳጅ ምክር ደስ ይላታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል። |
ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።
ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከሚባለው ሊቀበሉን ወጡ፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ልቡም ተጽናና።