Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 12:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ማርያምም ዋጋው ውድ የሆነ፣ ግማሽ ሊትር ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ አምጥታ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ እግሮቹንም በጠጕሯ አበሰች፤ ቤቱንም የሽቱው መዐዛ ሞላው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ማር​ያም ግን ዋጋዉ የከ​በ​ረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናር​ዶስ ሽቱ ወሰ​ደ​ችና የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እግር ቀባ​ችው፤ በፀ​ጕ​ሯም አሸ​ችው፤ የዚያ ሽቱ መዓ​ዛም ቤቱን መላው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 12:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለጌታ እንደማለ፥ ለያዕቆብም ኀያል እንደ ተሳለ፦


እርሷንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።


ንጉሡ በማዕዱ ሳለ፥ የእኔ ናርዶስ መዓዛውን ሰጠ።


ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።


እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ!


የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያምም መልካሙን ድርሻ መርጣለች፤ ከእርሷም አይወሰድባትም።”


አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርሷ ግን እግሬን ሽቶ ቀባች።


ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር።


ይህንም ብላ ሄደች፤ እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ “መምህር መጥቷል፤ እየጠራሽም ነው፤” አለቻት።


ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር፤” አለችው።


እንዲሁም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች