ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም እንዲሁ፥ ከሁለቱ ግን የሞኝ ቁጣ ይከብዳል።
ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤ የቂል ሰው ቍጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።
ድንጋይና አሸዋ ከባድ ናቸው፤ ሞኝ ሰው የሚያነሣሣው ቊጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።
ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።
የሰነፍ ቁጣ ቶሎ ይታወቃል፥ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
ሰነፍን በስንፍናው ከመገናኘት ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል።
ሌላ ያመስግንህ እንጂ ከአንተ አፍ አይውጣ፥ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይሁን።
ቁጣ ጭካኔን ያስከትላል፥ ንዴትም እንደ ጎርፍ ነው፥ በቅንዓት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?
አህያይቱም የጌታን መልአክ አየች፥ ከበለዓምም በታች ተምበርክካ ለጥ አለች፤ በለዓምም እጅግ ተቈጣ፥ አህያይቱንም በበትሩ ደበደባት።
ከክፉው እንደነበረው ወንድሙንም እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለምንስ ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ፥ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።