Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 12:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሰነፍ ቁጣ ቶሎ ይታወቃል፥ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ቂል ሰው ቍጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤ አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሞኝ ቊጣ ወዲያው ይታወቃል፤ ብልኅ ሰው ግን በእርሱ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ ችላ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 12:16
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሞኝ ሰው ቁጣውን ሁሉያለችግር ያወጣል፥ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርም የዘገየ፥ ለቁጣም የዘገየ ይሁን፤


ጥላቻ ክርክርን ታስነሣለች፥ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ትከድናለች።


ኃጢአትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፥ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆቹን ይለያያል።


ራሱን መቆጣጠር የማይችል ሰው፥ ቅጥር እንደሌለው እንደ ፈረሰ ከተማ ነው።


ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፥ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው።


በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች፥ በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም።


አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፥ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል።


ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም እንዲሁ፥ ከሁለቱ ግን የሞኝ ቁጣ ይከብዳል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች