ጠቢብ ሰው ብርቱ ነው፥ አዋቂም ሰው ኃይሉን ያበዛል።
ጠቢብ ሰው ታላቅ ኀይል አለው፤ ዕውቀት ያለውም ሰው ብርታትን ይጨምራል፤
ብርቱ ከመሆን ይልቅ ብልኅ መሆን ይሻላል፤ በእርግጥም ዕውቀት ከኀይል ይበልጣል፤
ጠቢብ ሰው ከብርቱ ይሻላል፥ ከታላቅ ርስትም ይልቅ ዕውቀት ያለው ይበልጣል።
በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ የምንጭ ቦታ ያደርጉታል፥ የበልግም ዝናብ በረከትን ይሰጣልና።
የጌታ መንገድ ያለ ነውር ለሚሄድ አምባ ነው፥ ክፋትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው።
ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥ የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል።
በመልካም አመራር ጦርነትን ትመራለህ፥ ብዙ ምክር ባለበትም ድል ይገኛል።
ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥ ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።
በከተማ ከሚኖሩ ከዐሥር ገዢዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢብን ታበረታለች።
ባዶ ቃል የጦር ስልትና ኃይል የሚሆንህ ይመስልህል? አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?
ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
እንደ ክብሩ ኃያልነት በሁሉ ኃይል እንድትበረቱና ሁሉንም ነገር በትዕግሥት በጽኑ ለመወጣት እንድትዘጋጁ እንዲሁም ደስ በመሰኘት