ምሳሌ 19:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድሀን ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፥ ይልቁንም ወዳጆቹ ከእርሱ ይርቃሉ። እነርሱንም በቃል ቢከተላቸው አንዳች አይረቡትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት! እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ ከቶ አያገኛቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኻን የገዛ ወንድሞቹ እንኳ ይጠሉታል፤ ወዳጆቹማ የበለጠ ያርቁታል፤ የቱንም ያኽል ቢጣጣር ወዳጆች አይኖሩትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም። |