መዝሙር 38:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና። ምዕራፉን ተመልከት |