ምሳሌ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው አፍ ቃል የጠለቀ ውኃ ነው፥ የጥበብም ምንጭ ፈሳሽ ወንዝ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤ የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰው አንደበት የሚወጣው የጥበብ ንግግር እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ እንደ ምንጭ ውሃም ጣፋጭ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥ የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው። |
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤