ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ፦ ባለ አእምሮ ነው ይባላል።
ቂል እንኳ ዝም ቢል ጠቢብ፣ አንደበቱንም ቢገዛ አስተዋይ ይመስላል።
ሞኝ ዝም ሲል ጥበበኛ ይመስላል፤ ምንም ሳይናገር ቢቀር እንደ ብልኅ ይቈጠራል።
አላዋቂ ጥበብን ቢጠይቅ ጥበብ ይሆነዋል፤ ዝም የሚል ሰውም ጥበበኛን ይመስላል።
ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር።
እነርሱ አልተናገሩምና፥ ቆመው ዳግመኛ አልመለሱምና እኔ በትዕግሥት እጠብቃለሁን?
የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል፥ የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል።
መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።
ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?
ደግሞም ሰነፍ በመንገድ ሲመላለስ እርሱ ልብ ይጐድለዋል፥ የሚያስበውም ሁሉ ስንፍና ነው።
አላዋቂዎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፥ የተሳልኸውን ፈጽመው።