Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሞኙም ቃልን ያበዛል። የሚመጣውን የሚያውቅ ሰው የለም፤ ከርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ሊነግረው ይችላል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሞኝ ሰው ልፍለፋ ያበዛል። ወደፊት የሚሆነውን የሚያውቅ የለም፤ ሰው ከሞተ በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያስረዳው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰነፍ ነገ​ርን ያበ​ዛል፤ ሰውም የሆ​ነ​ው​ንና ወደ ፊት የሚ​ሆ​ነ​ውን አያ​ው​ቅም፤ ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 10:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል፥ የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል።


የሚሆነውንም አያውቅም፥ እንዴትስ እንደሚሆን የሚነግረው ማን ነው?


ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?


አላዋቂዎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፥ የተሳልኸውን ፈጽመው።


ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚሰኝበት ነገር በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፥ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውንስ ወስዶ ማን ያሳየዋል?


በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


ስለዚህ ኢዮብ ከንቱ ንግግርን ከአፉ ያወጣል፥ ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል።”


በኃጢአቱም ላይ ዓመፅን ጨምሮአልና፥ በእኛም መካከል በፌዝ ያጨበጭባልና፥ እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ቃላትን ያበዛልና።”


በመልካም ቀን ደስ ይበልህ፥ በክፉም ቀን ተመልከት፥ ሰው ከእርሱ በኋላ መርምሮ ምንም እንዳያገኝ እግዚአብሔር ይህንንም ያንንም እንዲሁ ሠርቶአል።


ጻድቃንና ጠቢባን፥ ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅርም ሆነ ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፤ ሁሉም በፊታቸው ነው።


የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና።


በአፋችሁ ታበያችሁብኝ፥ ንግግራችሁንም በእኔ ላይ አበዛችሁ፤ እኔም ሰምቼዋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች