ምሳሌ 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፥ ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው ታጠፋቸዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅኖችን ትክክለኛነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶች ግን በገዛ አታላይነታቸው ይጠፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥተኞች ሰዎች ቅንነታቸው ይመራቸዋል። እምነት የማይጣልባቸው ሰዎች ግን ጠማማነታቸው ያጠፋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃንን ፍጻሜያቸው ትመራቸዋለች፤ ኃጥኣንን ግን መሰነካከላቸው ትማርካቸዋለች። |
ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።